ቁም ነገሮችን እና እና ሀይማኖታዊ ትምህርቶችን የያዘ
Recent Updates
 • ‹‹ባለንጀሮችህ አንድ ሺ ሊሆኑ ይችላሉ ያንተን ምስጢር ደብቆ የሚይዘው ግን አንድ ነው ::
  ባልንጀራ በማብዛት ለእግዚአብሔር ጊዜ አትጣ::››
  ቅዱስ ዩሐንስ አፈ-ወርቅ

  ‹‹ባለንጀሮችህ አንድ ሺ ሊሆኑ ይችላሉ ያንተን ምስጢር ደብቆ የሚይዘው ግን አንድ ነው :: ባልንጀራ በማብዛት ለእግዚአብሔር ጊዜ አትጣ::›› ቅዱስ ዩሐንስ አፈ-ወርቅ
  6
  4 Comments 0 Shares
 • “ስለ መተላለፋችን ምንም አይነት ቅጣት የማንቀበል ቢሆን ኖሮ እግዚአብሔር ሕሊናን የሚያህል ዳኛ በውስጣችን አይፈጥርም ነበር :: ”
  ቅዱስ አትናቴዎስ
  “ስለ መተላለፋችን ምንም አይነት ቅጣት የማንቀበል ቢሆን ኖሮ እግዚአብሔር ሕሊናን የሚያህል ዳኛ በውስጣችን አይፈጥርም ነበር :: ” ቅዱስ አትናቴዎስ
  9
  5 Comments 0 Shares
 • መሓረኒ ድንግል
  ወተሰሓለኒ በበዘመኑ
  መሓረኒ ድንግል ወተሰሓለኒ በበዘመኑ :heart: :heart: :heart:
  10
  6 3 Comments 0 Shares
 • ለሁሉም ጊዜ አለው
  🦻🦻🦻
  "ለሁሉ ዘመን አለው፥ ከሰማይ በታችም ለሆነ ነገር ሁሉ ጊዜ አለው። ለመወለድ ጊዜ አለው፥ ለመሞትም ጊዜ አለው፤ ለመትከል ጊዜ አለው፥ የተተከለውንም ለመንቀል ጊዜ አለው፤ለመግደል ጊዜ አለው፥ ለመፈወስም ጊዜ አለው፤ ለማፍረስ ጊዜ አለው፥ ለመሥራትም ጊዜ አለው፤
  ለማልቀስ ጊዜ አለው፥ ለመሳቅም ጊዜ አለው፤ ዋይ ለማለት ጊዜ አለው፥ ለመዝፈንም ጊዜ አለው፤
  ድንጋይን ለመጣል ጊዜ አለው፥ ድንጋይንም ለመሰብሰብ ጊዜ አለው፤ ለመተቃቀፍ ጊዜ አለው፥ ከመተቃቀፍም ለመራቅ ጊዜ አለው፤ለመፈለግ ጊዜ አለው፥ ለማጥፋትም ጊዜ አለው፤ ለመጠበቅ ጊዜ አለው፥ ለመጣልም ጊዜ አለው፤
  ለመቅደድ ጊዜ አለው፥ ለመስፋትም ጊዜ አለው፤ ዝም ለማለት ጊዜ አለው፥ ለመናገርም ጊዜ አለው፤
  ለመውደድ ጊዜ አለው፥ ለመጥላትም ጊዜ አለው፤ ለጦርነት ጊዜ አለው፥ ለሰላምም ጊዜ አለው። "
  መጽሐፈ መክብብ 3 ÷ 1-8
  ጠቢቡ ሶሎሞን እንዳለው ለሁሉም ጊዜ አለው፡፡ ያለጊዜው የሚሆን እና የሚፈፀም ነገር የለም ይህንንም የሚወስነው እግዚአብሔር ብቻ ነው ፡፡ ጊዜው ካልሆነ ማናችንም ብንሆን የምንፈልገውን ነገር በምንፈልገው ሰአት ማድረግ አይቻልም፣ ነገር ግን እግዚአብሔር በፈቀደው ሰአት እንደሚሆን ተስፋ ሊኖረን ይገባል፡፡ ምንም እንኳን ዛሬ ብንከፋ ፣ ባስቸጋሪ፣ በሚያጨንቅ ፣ በሚደብር ሁኔታ ውስጥ ብንሆን ፣ ሰዎች ቢክዱን ፣ ቢገፉን ልባችንን ቢያደሙት ሳይበድት የሚክስ ክርስቶስ ስላለ እንጠብቅ ፡፡ ሰው የዘራውን ነው የሚያጭደው ፡፡ ሁሉም የስራውን ያገኛል ፡፡ መታገስ ፣ መታገስ ፣ መታገስ የበለጠ ዋጋ አለው፡ እግዚአብሔርን የሆነ ነገር ጠይቀነው ዝም ካለ የጠየቅነው ስለማይጠቅመን ወይ ደግሞ የጠየቅነው ትንሽ ሆኖ የበለጠ ሊሰጠን ነው፡፡ ከ እኛ የሚጠበቀው እርሱን ማመን እና በተስፋ መጠበቅ ነው ፡፡ እግዚአብሔር አይዘገይም ፣ አይቸኩልምም ፡፡ አንድ ቀን ቀና ያደርገናል ፣ በደስታ ፣ በፍቅር ያንበሸብሸናል፡፡ ብቻ መጠበቅ !!!
  ተስፋ ለሰው ልጅ መሰረታዊ ነገር ነው ፡፡ ባለን ነገር ማመስገን ፣ መፀለይ ፣ መልካም ነገር ማድረግ ሰዎች እንዳያዝኑብን እና እንዳያለቅሱብን ማስደሰት እንኳን ባንችል ላለማስከፋት መሞከር " የጭንቀት ቀን ሳይመጣ በጕብዝናህ ወራት ፈጣሪህን አስብ፤ ደስ አያሰኙም የምትላቸውም ዓመታት ሳይደርሱ" እንዳለ ጠቢቡ ሶሎሞን
  በወጣትነት እድሜአችን የሚጠበቅብንን ነገር ማድረግ፣ ለራሳችን ባለን ነገር ደስታ መፍጠር ፣ በየጊዜው መንፈሳዊ ልምምድ ማድረግ እና ሰው ለሞሆን መጣር ነው ከእኛ የሚጠበቀው ቀሪውን ለፈጣሪ መስጠት አለብን ፡፡ በእኛ ሀይል አንዳች የሚሆን ነገር የለም ፡፡ እግዚአብሔርን ማማረር መፈታተን አይገባም፡፡ ቸርነቱን ብቻ ማሰብ እንጂ ባማረርን ቁጥር ችግራችን ይጨምራል፡፡ በማመስገን እንጂ በማማረር ችግሩ የተፈታለት ሰው አላየንም አልሰማንም፡፡🙅‍♂️🙅‍♂️🙅‍♂️
  " ነገር ግን አስቀድማችሁ የእግዚአብሔርን መንግሥት ጽድቁንም ፈልጉ፥ ይህም ሁሉ ይጨመርላችኋል።"
  የማቴዎስ ወንጌል 6 ÷ 33
  መልካም መልካሙን ካደረግን እና ካሰብን ሌላው ለእግዚአብሔር ቀላል ነው ካሰብነው በላይ ይጨመርልናል፡፡
  ሁሉንም በጊዜው የሚያከናውን አምላክ ትዕግስትን እና ማስተዋልን ሰጥቶን ቀናችን እንድንጠብቅ ይርዳን
  አሜን!!!
  🤲🤲🤲


  ለሁሉም ጊዜ አለው 🦻🦻🦻 "ለሁሉ ዘመን አለው፥ ከሰማይ በታችም ለሆነ ነገር ሁሉ ጊዜ አለው። ለመወለድ ጊዜ አለው፥ ለመሞትም ጊዜ አለው፤ ለመትከል ጊዜ አለው፥ የተተከለውንም ለመንቀል ጊዜ አለው፤ለመግደል ጊዜ አለው፥ ለመፈወስም ጊዜ አለው፤ ለማፍረስ ጊዜ አለው፥ ለመሥራትም ጊዜ አለው፤ ለማልቀስ ጊዜ አለው፥ ለመሳቅም ጊዜ አለው፤ ዋይ ለማለት ጊዜ አለው፥ ለመዝፈንም ጊዜ አለው፤ ድንጋይን ለመጣል ጊዜ አለው፥ ድንጋይንም ለመሰብሰብ ጊዜ አለው፤ ለመተቃቀፍ ጊዜ አለው፥ ከመተቃቀፍም ለመራቅ ጊዜ አለው፤ለመፈለግ ጊዜ አለው፥ ለማጥፋትም ጊዜ አለው፤ ለመጠበቅ ጊዜ አለው፥ ለመጣልም ጊዜ አለው፤ ለመቅደድ ጊዜ አለው፥ ለመስፋትም ጊዜ አለው፤ ዝም ለማለት ጊዜ አለው፥ ለመናገርም ጊዜ አለው፤ ለመውደድ ጊዜ አለው፥ ለመጥላትም ጊዜ አለው፤ ለጦርነት ጊዜ አለው፥ ለሰላምም ጊዜ አለው። " መጽሐፈ መክብብ 3 ÷ 1-8 ጠቢቡ ሶሎሞን እንዳለው ለሁሉም ጊዜ አለው፡፡ ያለጊዜው የሚሆን እና የሚፈፀም ነገር የለም ይህንንም የሚወስነው እግዚአብሔር ብቻ ነው ፡፡ ጊዜው ካልሆነ ማናችንም ብንሆን የምንፈልገውን ነገር በምንፈልገው ሰአት ማድረግ አይቻልም፣ ነገር ግን እግዚአብሔር በፈቀደው ሰአት እንደሚሆን ተስፋ ሊኖረን ይገባል፡፡ ምንም እንኳን ዛሬ ብንከፋ ፣ ባስቸጋሪ፣ በሚያጨንቅ ፣ በሚደብር ሁኔታ ውስጥ ብንሆን ፣ ሰዎች ቢክዱን ፣ ቢገፉን ልባችንን ቢያደሙት ሳይበድት የሚክስ ክርስቶስ ስላለ እንጠብቅ ፡፡ ሰው የዘራውን ነው የሚያጭደው ፡፡ ሁሉም የስራውን ያገኛል ፡፡ መታገስ ፣ መታገስ ፣ መታገስ የበለጠ ዋጋ አለው፡ እግዚአብሔርን የሆነ ነገር ጠይቀነው ዝም ካለ የጠየቅነው ስለማይጠቅመን ወይ ደግሞ የጠየቅነው ትንሽ ሆኖ የበለጠ ሊሰጠን ነው፡፡ ከ እኛ የሚጠበቀው እርሱን ማመን እና በተስፋ መጠበቅ ነው ፡፡ እግዚአብሔር አይዘገይም ፣ አይቸኩልምም ፡፡ አንድ ቀን ቀና ያደርገናል ፣ በደስታ ፣ በፍቅር ያንበሸብሸናል፡፡ ብቻ መጠበቅ !!! ተስፋ ለሰው ልጅ መሰረታዊ ነገር ነው ፡፡ ባለን ነገር ማመስገን ፣ መፀለይ ፣ መልካም ነገር ማድረግ ሰዎች እንዳያዝኑብን እና እንዳያለቅሱብን ማስደሰት እንኳን ባንችል ላለማስከፋት መሞከር " የጭንቀት ቀን ሳይመጣ በጕብዝናህ ወራት ፈጣሪህን አስብ፤ ደስ አያሰኙም የምትላቸውም ዓመታት ሳይደርሱ" እንዳለ ጠቢቡ ሶሎሞን በወጣትነት እድሜአችን የሚጠበቅብንን ነገር ማድረግ፣ ለራሳችን ባለን ነገር ደስታ መፍጠር ፣ በየጊዜው መንፈሳዊ ልምምድ ማድረግ እና ሰው ለሞሆን መጣር ነው ከእኛ የሚጠበቀው ቀሪውን ለፈጣሪ መስጠት አለብን ፡፡ በእኛ ሀይል አንዳች የሚሆን ነገር የለም ፡፡ እግዚአብሔርን ማማረር መፈታተን አይገባም፡፡ ቸርነቱን ብቻ ማሰብ እንጂ ባማረርን ቁጥር ችግራችን ይጨምራል፡፡ በማመስገን እንጂ በማማረር ችግሩ የተፈታለት ሰው አላየንም አልሰማንም፡፡🙅‍♂️🙅‍♂️🙅‍♂️ " ነገር ግን አስቀድማችሁ የእግዚአብሔርን መንግሥት ጽድቁንም ፈልጉ፥ ይህም ሁሉ ይጨመርላችኋል።" የማቴዎስ ወንጌል 6 ÷ 33 መልካም መልካሙን ካደረግን እና ካሰብን ሌላው ለእግዚአብሔር ቀላል ነው ካሰብነው በላይ ይጨመርልናል፡፡ ሁሉንም በጊዜው የሚያከናውን አምላክ ትዕግስትን እና ማስተዋልን ሰጥቶን ቀናችን እንድንጠብቅ ይርዳን አሜን!!! 🤲🤲🤲
  11
  3 Comments 0 Shares
 • 9
  4 3 Comments 0 Shares
 • ትንቢት ይሆን?
  ሀገራችንን እያመሳት ካሉ ነገሮች አንዱ social media ነዉ ለዛዉም በነጮች የሚዘወር social media ግፍ ሲሰራጭ ዝም ብሎ የሚያይ ሜዲያ አሁን ግን ያ ተቀይሯል ሀገር በቀል የሆነና የሀገርን እሴት ያልጣሰ ሁሉን ያጣመረ ኢትዮጵያዊ social media ተፈጥሯልና ደስ ሊለን ይገባል
  ቻጦጵያ chatopia
  6
  3 Comments 0 Shares
 • ሰው ሆይ! የሚጎዳህ ሀብትህ አይደለም፤ ድኽነትህም አይደለም። ሰውን የሚጎዳው ክፉ ልብ ነው። ክፉ ልብ ደግሞ በሀብትም፣ ሀብት በማጣትም የሚመጣ አይደለም። ክፉ ልብ ሌሎች ክፉ ልቦችን ይወልዳል። እሳት እሳትን እየወለደ ብዙ እንጨቶችን እንደሚበላ ኹሉ ክፉ ልብም እንደዚህ ነው።

  አንተ ሰው! ይህን ማወቅ ትወዳለህን? ክፉ ምግባር ወይም በጎ ምግባር በተፈጥሮ የሚገኙ አይደሉም። እነዚህ ኹለቱ ከክፉ ልብ ወይም ከመልካም ልብ የሚገኙ ናቸው።

  © ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ፥ አምስቱ የንስሓ መንገዶች፥ ገጽ 9
  ሰው ሆይ! የሚጎዳህ ሀብትህ አይደለም፤ ድኽነትህም አይደለም። ሰውን የሚጎዳው ክፉ ልብ ነው። ክፉ ልብ ደግሞ በሀብትም፣ ሀብት በማጣትም የሚመጣ አይደለም። ክፉ ልብ ሌሎች ክፉ ልቦችን ይወልዳል። እሳት እሳትን እየወለደ ብዙ እንጨቶችን እንደሚበላ ኹሉ ክፉ ልብም እንደዚህ ነው። አንተ ሰው! ይህን ማወቅ ትወዳለህን? ክፉ ምግባር ወይም በጎ ምግባር በተፈጥሮ የሚገኙ አይደሉም። እነዚህ ኹለቱ ከክፉ ልብ ወይም ከመልካም ልብ የሚገኙ ናቸው። © ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ፥ አምስቱ የንስሓ መንገዶች፥ ገጽ 9
  9
  8 Comments 0 Shares
 • 9
  5 3 Comments 0 Shares
 • ሰኔ 12 2013 ዓ.ም በየካ ደብረ ሳህል ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲን

  ሰኔ 12 2013 ዓ.ም በየካ ደብረ ሳህል ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲን
  15
  10 Comments 0 Shares
 • ጾመ ሐዋርያት
  ጾም ማለት ሰውነት ከሚፈልጋቸው ነገር ሁሉ መከልከል ማለት ነው፡፡ ወይም ለሥጋ የሚመቸውን ነገር መተው ማለት ነው፡፡
  የብሉይ ኪዳን ነቢያት ከእግዚአብሔር ጋር በሚገናኙበት ወራት እህል ውኃ ለአፋቸው አይገባም ነበር፡፡
  /ዘዳ 34፥28/ በኃጢአታቸው ብዛት የመጣባቸው መዓት የሚመልሰው ቁጣውም የሚበረደው ሕዝቡ በጾም ሲለምኑትና ሲማልዱት ነበር፡፡ /ዮና 3፥5-10/፡
  በአዲስ ኪዳንም ራሱ መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመዋዕል ሥጋዌው መጀመሪያ አድርጎ የሠራው ሕግ ነው፡፡ /ማቴ 4፥21/ ጌታችን በስስት በፍቅረ ንዋይና በትዕቢት የሚመጣበትን ጠላት ዲያብሎስ በጾም ድል እንድምንነሣው አሳይቶናል፡፡ ይህም ብቻ ሳይሆን በቁራኝነት አብሮ የሚኖር ጠላት ሰይጣንን በጾም የሚወገድ መሆኑን መድኃኒታችን ተናግሯል /ማቴ 17፥21/፡
  ስብከተ ወንጌል የሚያገለግሉ ዲያቆናትና ቀሳውስት የሚሾሙትም በጾምና በጸሎት ነበር፡፡ /የሐዋ13፥3፤4፥25/
  እነ ቅዱስ ቆርኔሌዎስ ያላሰቡትን ክብር ያገኙት በጾማና በጸሎት ፈጣሪያቸው ማልደው ነው /የሐዋ 10፥20/
  ጾም እንኳን የጠበቅነውንና ያሰብነውን ቀርቶ ያላሰብነውንና ያልጠበቅነውን ፈጽሞም የማይገባንን ጸጋና ክብር የሚያሰጥ ነው፡ በሐዋርያት መሠረት ላይ የተመሠረተች የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን የጾም ሕግና ሥርዓት አላት እነዚህም የፈቃድና የአዋጅ አጽዋማት ይባላሉ፡፡ ከሰባቱ የአዋጅ አጽዋማት አንዱ የሐዋርያት (የሰኔ) ፆም ነው፡፡
  ጾመ ሐዋርያት ጾም ማለት ሰውነት ከሚፈልጋቸው ነገር ሁሉ መከልከል ማለት ነው፡፡ ወይም ለሥጋ የሚመቸውን ነገር መተው ማለት ነው፡፡ የብሉይ ኪዳን ነቢያት ከእግዚአብሔር ጋር በሚገናኙበት ወራት እህል ውኃ ለአፋቸው አይገባም ነበር፡፡ /ዘዳ 34፥28/ በኃጢአታቸው ብዛት የመጣባቸው መዓት የሚመልሰው ቁጣውም የሚበረደው ሕዝቡ በጾም ሲለምኑትና ሲማልዱት ነበር፡፡ /ዮና 3፥5-10/፡ በአዲስ ኪዳንም ራሱ መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመዋዕል ሥጋዌው መጀመሪያ አድርጎ የሠራው ሕግ ነው፡፡ /ማቴ 4፥21/ ጌታችን በስስት በፍቅረ ንዋይና በትዕቢት የሚመጣበትን ጠላት ዲያብሎስ በጾም ድል እንድምንነሣው አሳይቶናል፡፡ ይህም ብቻ ሳይሆን በቁራኝነት አብሮ የሚኖር ጠላት ሰይጣንን በጾም የሚወገድ መሆኑን መድኃኒታችን ተናግሯል /ማቴ 17፥21/፡ ስብከተ ወንጌል የሚያገለግሉ ዲያቆናትና ቀሳውስት የሚሾሙትም በጾምና በጸሎት ነበር፡፡ /የሐዋ13፥3፤4፥25/ እነ ቅዱስ ቆርኔሌዎስ ያላሰቡትን ክብር ያገኙት በጾማና በጸሎት ፈጣሪያቸው ማልደው ነው /የሐዋ 10፥20/ ጾም እንኳን የጠበቅነውንና ያሰብነውን ቀርቶ ያላሰብነውንና ያልጠበቅነውን ፈጽሞም የማይገባንን ጸጋና ክብር የሚያሰጥ ነው፡ በሐዋርያት መሠረት ላይ የተመሠረተች የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን የጾም ሕግና ሥርዓት አላት እነዚህም የፈቃድና የአዋጅ አጽዋማት ይባላሉ፡፡ ከሰባቱ የአዋጅ አጽዋማት አንዱ የሐዋርያት (የሰኔ) ፆም ነው፡፡
  16
  4 Comments 0 Shares
More Stories